am_tn/deu/28/23.md

995 B

ሰማይ ናስ ይሆናል

ሙሴ ዝናብ ስለማይኖር ሰማዩ እንደ ናስ እንደሚሆን ይናገራል። አ.ት፡ “ሰማይ -- ዝናብን አይሰጥም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ምድር -- ብረት ትሆናለች

ሙሴ ምድር ምንም ሰብል ስለማይበቅልባት እንደ ብረት እንደምትሆን ይናገራል። አ.ት፡ “መሬቱ ላይ ምንም ነገር አይበቅልም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የምድርህን ዝናብ እግዚአብሔር ወደ ትቢያና አቧራ ይለውጠዋል

“እግዚአብሔር በዝናብ ምትክ አሸዋ አዘል ውሽንፍር ይልካል”

እስክትጠፋ ድረስ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እስኪያጠፋህ ድረስ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)