am_tn/deu/28/22.md

843 B

ተላላፊ በሽታ፣ ትኩሳት፣ በሰውነት መመረዝ

“በሽታና የሚያቃጥል ትኩሳት ያደክምሃል”። እነዚህ ሁሉ የሚያመለክቱት ሰዎች እንዲዳከሙና እንዲሞቱ የሚያደርጋቸውን በሽታ ነው።

በድርቅ

“በዝናብ እጥረት”

ዋግ

በሰብል ላይ የሚበቅል ሻጋታ ሲሆን እንዲበሰብሱ ያደርጋቸዋል

እነዚህ ያሳድዱሃል

ሙሴ በእስራኤላውያን ላይ ስለሚደርስባቸው ክፉ ነገሮች ሲናገር ከእስራኤላውያን በስተኋላ ሆነው በሚያሳድዱ ሰዎች ወይም እንስሶች አስመስሎ ይናገራል። አ.ት፡ “በእነርሱ ምክንያት ትሰቃያለህ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)