am_tn/deu/28/18.md

1.2 KiB

የተረገመ ይሆናል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይረግማል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የአካልህን ፍሬ፣ የመሬትህን ፍሬ

ይህ “ልጆችህ፣ ሰብልህ” ለሚለው የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በዘዳግም 28፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የከብትህ፣ የበግና የፍየል ጠቦቶችህ ብዛት

ይህ ጥምረት እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን እንስሳ ብዙና ብርቱ እንደሚያደርጋቸው በሁለት መንገድ የተነገረበት ነው። አ.ት፡ “የከብቶቹ ጥጃዎች፣ የበግና የፍየል መንጋው ጠቦቶች” (See: Doublet)

በምትገባበት ጊዜ -- በምትወጣበት ጊዜ

ይህ ጥምረት የሚያመለክተው በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚሆነውን የሕይወት ተግባራት በሙሉ ነው። ይህንን በዘዳግም 28፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (See: Merism)