am_tn/deu/28/13.md

1.5 KiB

ራስ እንጂ ጅራት አትሆንም

ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር የእስራኤልን ሕዝብ እንደ እንስሳ ይገልጸዋል፣ ይኸውም እስራኤላውያን ሁልጊዜ የሌሎች ሕዝቦች መሪዎች ይሆናሉ እንጂ ከቶም አገልጋዮቻቸው ለመሆን ከኋላ አይከተሉም ማለት ነው። እስራኤላውያን በኃይል፣ በገንዘብና በክብር ብልጫ ያላቸው ይሆናሉ። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከላይ ብቻ ይሆናሉ -- ፈጽሞ ከበታች አይሆኑም

እስራኤላውያን በሌሎች ላይ ገዢዎች ይሆናሉ እንጂ ሌሎች አይገዟቸውም።

እኔ አዛችኋለሁ

ሙሴ የሚናገረው ለእስራኤላውያን በሙሉ ነው፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)

እኔ ዛሬ ከማዝህ ቃል ሁሉ ሌሎች አማልክትን ተከትለህ ለማገልገል ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ካልተከተልክ

እግዚአብሔርን አለመታዘዝና ሌሎች አማልክትን ማምለክ ልክ አንድ ሰው በአካሉ ከእግዚአብሔር ቃል ተመልሶ በሌላ አቅጣጫ እንደ ሄደ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን በማገልገል ዛሬ እኔ የማዝህን ባትታዘዝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)