am_tn/deu/28/09.md

1015 B

እግዚአብሔር ለራሱ የተለየ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል

እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ የራሱ እንዲሆን በተለየ ሁኔታ መምረጡ ሌሎች ሕዝቦች በሙሉ ከሚኖሩበት ስፍራ ልዩ በሆነ ቦታ እግዚአብሔር እንዳስቀመጣቸው ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ለእርሱ የሚሆን ቅዱስ ሕዝብ ያደርግሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእግዚአብሔር ስም ተጠርተሃል

እዚህ ጋ “በእግዚአብሔር ስም ተጠርተሃል” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም የእርሱ መሆን ማለት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የራሱ አድርጎ ጠርቶሃል” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)