am_tn/deu/28/07.md

1.5 KiB

በላይህ ላይ የተነሣውን ጠላትህን በፊትህ ተመትቶ እንዲወድቅ ያደርገዋል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሚዋጉህን ጠላቶችህን እንድታሸንፋቸው ያደርግሃል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ሆኖም በሰባት መንገድ ከአንተ ይሸሻሉ

“ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከአንተ በሩጫ ይሸሻሉ”

ሰባት መንገድ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ትክክለኛው ቁጥር ከሰባት ሊበልጥ ወይም ሊያንስ ይችላል። አ.ት፡ “በብዙ የተለያዩ አቅጣጫዎች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በረከት በጎተራህ እንዲመጣ እግዚአብሔር ያዘዋል

እግዚአብሔር አንድ ሰው በድንገት እስራኤላውያንን እንዲያጠቃቸው የሚያዝ በሚመስል መልኩ እግዚአብሔር እንደሚባርካቸው ሙሴ ያብራራል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በሚባርክህ ጊዜ በጎተራህ ባለው ጥራጥሬ ብዛት ትገረማለህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

እጅህን በምታኖርበት ሁሉ ላይ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ነገር ሁሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)