am_tn/deu/28/03.md

1.2 KiB

ትባረካለህ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይባርክሃል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በከተማ - በእርሻ

ይህ ቁንጽል፣ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ይባርካቸዋል የሚል ትርጉም አለው። (See: Merism)

የአካልህ ፍሬ፣ የመሬትህ ፍሬ፣ የእንስሳህ ፍሬ

“ልጆችህ፣ ሰብልህ፣ እና እንስሶችህ” እነዚህ የአነጋገር ዘይቤዎች እስራኤላውያን ዋጋ ለሚሰጧቸው ነገሮች በሙሉ በቁንጽል አመልካቾች ናቸው። (የአነጋገር ዘይቤ እና Merism የሚለውን ተመልከት)

የእንስሳህ ፍሬ፣ የከብቶችህ ፍሬ፣ እና የበግና የፍየል ጠቦቶችህ

ይህ ጥምረት እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን እንስሶች እንደሚያበዛቸውና እንደሚያበረታቸው በሦስት መንገድ መናገሪያ ነው። አ.ት፡ “የከብቶቻችሁ ጥጃዎች እና የበግና የፍየል መንጋ ጠቦቶቻችሁ ከእንስሶቻችሁ ሁሉ ጋር” (See: Doublet)