am_tn/deu/27/18.md

1.3 KiB

ሰውየው የተረገመ ይሁን

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 27፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰውየውን ይርገመው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ለመጻተኛው፣ -- ለመበለቲቱ የሚገባውን ፍትሕ ጉልበቱን ተጠቅሞ የሚነጥቅ

ሙሴ ስለ ፍትሕ የሚናገረው አንድ ጉልበተኛ የሆነ ሰው ደካማ ከሆነው ሰው ላይ በኃይል እንደሚቀማው አካላዊ ቁስ አድርጎ ነው። የአንተ ቋንቋ ምናልባት “ጉልበቱን ተጠቅሞ የሚነጥቅ” ለማለት የሚያስችል አንድ ቃል ይኖረው ይሆናል። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 24፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “መጻተኛውን -- መበለቲቱን የሚበድል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አባቶቻቸውን ያጡ ልጆች

እነዚህ ሁለቱም ወላጆቻቸው የሞቱባቸውና የሚንከባከባቸው ዘመድ የሌላቸው ልጆች ናቸው።