am_tn/deu/26/16.md

1.1 KiB

በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ

እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚመለከቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህ ሁለት ሐረጎች በአንድ ላይ “ሙሉ በሙሉ” ወይም “በቅንነት” ለማለት ጥቅም ላይ ውለዋል። ይህንን በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)

በመንገዶቹ ትሄድና ሥርዓቱን፣ ትዕዛዛቱን እና ሕጉን ትጠብቅ ዘንድ፣ ድምፁንም ትሰማ ዘንድ

እዚህ ጋ “መሄድ”፣ “መጠበቅ” እና “መስማት” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚያመለክተው እግዚአብሔር የተናገረውን ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ያዘዘው ሁሉ ሙሉ በሙሉ እንድትጠብቅ” (See: Parallelism and Metonymy)