am_tn/deu/26/14.md

1.9 KiB

በለቅሶዬ ጊዜ ከእርሱ ምንም አልበላሁም

“ባለቀስኩበት ወቅት የትኛውንም አስራት አልበላሁም”

ባልነጻሁበት ጊዜ

እዚህ ጋ “ያልነጻ” ማለት በሕጉ መሠረት ንጹሕ ያልሆነ ሰው ማለት ነው። ንጹሕ ያልሆነ ሰው ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን አስራት እንዲነካ እግዚአብሔር አይፈቅድለትም”። የዚህ አነጋገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በሕጉ መሠረት ንጹሕ ባልነበርኩበት ጊዜ” ወይም “ልነካው እንደማልችል ሕጉ በሚናገርበት ጊዜ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

የአምላኬን የእግዚአብሔርን ድምፅ ሰምቻለሁ፤ እንዳደርገው ያዘዝከኝን ሁሉንም ነገር ታዝዣለሁ

እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” እግዚአብሔር ለተናገረው የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ሁለቱም አነጋገሮች ተመሳሳይ ትርጉም ይጋራሉ። ሰውየው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በሙሉ ስለመታዘዙ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Parallelism የሚለውን ተመልከት))

ከምትኖርበት ከቅዱሱ ስፍራ፣ ከሰማይ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ነው። አ.ት፡ “ከቅዱስ ማደሪያህ፣ ከሰማይ” (See: Dou- blet)

ወተትና ማር የምታፈስ ምድር

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በዘዳግም 6፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ብዙ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር” ወይም “ከብት ለማርባትና ለእርሻ ምርጥ የሆነች ምድር”