am_tn/deu/26/08.md

1.2 KiB

እግዚአብሔር አመጣን

እዚህ ጋ “እኛ” የሚያመለክተው በግብፅ ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤል ሕዝብ ነው። ተናጋሪው በግብፅ ቢኖርም ባይኖርም ራሱን ከሕዝቡ አንዱ አድርጎ ይጨምራል። (See: Inclusive “We”)

በብርቱ እጅ፣ በተዘረጋች ክንድ

እዚህ ጋ “ብርቱ እጅ” እና “የተዘረጋች ክንድ” የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያመለክቱ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ብርቱ ኃይሉን በማሳየት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በታላቅ ማስደንገጥ

“ያዩአቸውን ሰዎች በሚያስፈሩ ድርጊቶች”

ወተትና ማር የምታፈስ ምድር

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በዘዳግም 6፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡ አ.ት፡ “ብዙ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር” ወይም “ከብት ለማርባትና ለእርሻ ምርጥ የሆነች ምድር”