am_tn/deu/26/05.md

1.1 KiB

ቅድመ ቅድም አያቴ ተቅበዝባዥ አራማዊ ነበር

ይህ እስራኤላዊ ወንድ ቅርጫቱን በሚያቀርብበት ጊዜ መናገር የሚኖርበት የዐረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ነው።

ተቅበዝባዥ አራማዊ

ይህ የእስራኤላውያኑ ሁሉ ቅድመ ቅድም አያት የነበረውን ያዕቆብን ያመለክታል። እርሱ ለብዙ ዓመታት በሶሪያ በሚገኝ በአራም ናሃሪም ይኖር ነበር።

በዚያ ቆየ

“ቀሪ ሕይወቱን በዚያ ኖሯል”

በዚያ እርሱ -- ሆነ

“እርሱ” የሚለው ቃል “የያዕቆብን ተወላጆች” የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ታላቅ፣ ኃያል

በመሠረቱ እነዚህ ቃላት የሚሉት አንድ ነገር ነው። እስራኤል ብዙና ኃይለኛ ሕዝብ መሆኑ ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “በጣም ታላቅ” (See: Doublet)