am_tn/deu/25/17.md

1.7 KiB

አማሌቅ ያደረገብህ ትዝ ይበልህ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን “አማሌቅ” አማሌቃውያን ሰዎችን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አማሌቃውያን ያደረጉብህን አስታውስ” (የአነጋገር ዘይቤ፣ ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በወጣህ ጊዜ

እዚህ ጋ “አንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)

በመንገድ ላይ እንዴት እንደተገናኘህ

“በጉዞ ላይ እያለህ እንዴት እንደተገናኙህ”

ከኋላ የነበራችሁትን አጠቋችሁ

“የኋላ መስመር ላይ የነበሩትን ሰዎችህን አጠቃ”

ከበስተኋላህ የደከሙትን ሁሉ

“በኋለኛው መስመር ላይ ደካሞች የነበሩትን ሰዎች በሙሉ”

ዝለትና ድካም

እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ሕዝቡ ምን ያህል ደክመው እንደነበሩ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ደክመውና ዝለው” (See: Doublet)

ለእግዚአብሔር ክብርን አልሰጠም

የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን ቅጣት አልፈራም” ወይም “እግዚአብሔርን አላከበረም” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ደምስስ

“ከእንግዲህ ማንም እንዳያስታውሳቸው አማሌቃውያንን በሙሉ ግደላቸው”