am_tn/deu/25/05.md

1.4 KiB

ወንድማማቾች በአንድነት የሚኖሩ ከሆነ

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፣ 1) “ወንድማማቾች በአንድ ንብረት ላይ የሚኖሩ ከሆነ” ወይም 2) “ወንድማማቾች ተቀራርበው የሚኖሩ ከሆነ”

ያን ጊዜ የሟቹ ሰው ሚስት ሌላ ሰው ማግባት አይኖርባትም

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ያን ጊዜ የሟች ቤተሰቦች መበለቲቱ ሌላ ሰው እንድታገባ መፍቀድ የለባቸውም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የዋርሳነቱን ተግባር ይፈጽምላት

“የሟች ወንድም እንዲያደርግ የሚጠበቅበትን ያድርግ”

በሟች ወንድሙ ስም ይጠራል

“ስም” የሚለው ቃል የሰውየውን የቤተሰብ ሐረግ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የሟች ወንድሙ የቤተሰብ ሐረግ ይቀጥላል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስሙ ከእስራኤል እንዳይጠፋ

“ስም” የሚለው ቃል የሰውየውን የቤተሰብ ሐረግ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የቤተሰቡ ሐረግ ከእስራኤል እንዳይጠፋ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)