am_tn/deu/24/19.md

1.8 KiB

ከእርሻህ ላይ የደረሰውን ሰብል በምትሰበስብበት ጊዜ

“በእርሻህ ውስጥ ሰብል በምታጭድበት ጊዜ”

የእህል ነዶ

አንዳንድ ትርጉሞች ይህንን እንደ “እስር” ይተረጉሙታል። ትርጉሞቹ ሁሉ የሚያመለክቱት በቀላሉ ለመሸከም የሚቻል፣ በይበልጥም በአንድ ላይ የታሰሩ የአገዳ እህሎችን ነው።

እርሱ ለመጻተኞች፣ አባቶቻቸውን ላጡ ልጆች ወይም ለመበለቶች ይሁን

የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ነዶውን መጻተኛው፣ ወላጆቹን ያጣው ወይም መበለቲቱ እንዲወስዱት ተወው” (See: Ellipsis)

በእጆችህ ሥራ ሁሉ

እዚህ ጋ “እጆች” የሚያመለክቱት ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ሥራ ሁሉ” (See: Synecdoche)

የወይራ ዛፍህን በምትነቀንቅበት ጊዜ

የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ፍሬው ሲረግፍ ለማንሣት የወይራ ዛፍህን ቅርንጫፎች በምትነቀንቅበት ጊዜ” (See: Ellipsis)

በድጋሚ ወደ ቅርንጫፎቹ አትመለስ

“ከወይራ ዛፉ ላይ እያንዳንዱን ፍሬ አትልቀም”

እርሱ ለመጻተኞች፣ አባቶቻቸውን ላጡ ልጆች ወይም ለመበለቶች ይሆናል

የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “በቅርንጫፎቹ ላይ የሚቀሩት የወይራ ፍሬዎች መጻተኞች፣ ወላጆቻቸውን ያጡና መበለቶች ለቅመው የሚወስዷቸው ናቸው” (See: Ellipsis)