am_tn/deu/22/20.md

1.8 KiB

ሆኖም ይህ ነገር እውነት ቢሆን

“ሆኖም እውነት ቢሆን” ወይም “ሆኖም ሰውየው የተናገረው እውነት ቢሆን”

በልጅቱ ላይ የድንግልና ማስረጃ ባይገኝ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰውየው ልጅቱ ድንግል ስለመሆኗ ማረጋገጫ አላገኘም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የድንግልና ማረጋገጫ

የነገር ስም የሆኑት “ማረጋገጫ” እና “ድንግልና” እንደ ግሣዊ ሐረጎች ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “ልጅቱ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽማ እንደማታውቅ የሚያስረዳ አንዳች ነገር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ከዚያም ልጅቱን ያውጧት

“ከዚያም ሽማግሌዎቹ ልጅቱን ያውጧት”

በድንጋይ ወግረው ይግደሏት

“እስክትሞት ድረስ ድንጋይ ወርውሩባት”

በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ተግባር ፈጽማለችና

“በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ነገር አድርጋለችና”

በአባቷ ቤት ውስጥ እንደ ሴተኛ አዳሪ ለማድረግ

“በአባቷ ቤት ውስጥ እየኖረች እንደ ሴተኛ አዳሪ ማድረግ”

ክፉን አስወግድ

ቅጽል የሆነው “ክፉ” እንደ ስማዊ ሐረግ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይህንን ክፉ ነገር ያደረገውን ከእስራኤላውያን መካከል አስወግድ” ወይም “ይህንን ክፉ ሰው አስወግደው” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)