am_tn/deu/22/09.md

1013 B

ምርትህ በሙሉ በተቀደሰው ስፍራ እንዳይወረስ

“ቅዱስ ስፍራ” የሚለው ቃል በተቀደው ስፍራ የሚሠሩትን ካህናት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ቅዱስ ስፍራ ያሉ ካህናት ምርቱን ሁሉ እንዳይወስዱት” ወይም “ምርቱን ሁሉ እንዳታረክሰውና ካህናቱ ከመጠቀም እንዳይከለክሉህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በወይን ተክል ቦታ የሚበቅለውን

“በወይን ተክል ቦታ የሚበቅለውን ፍሬ”

ሱፍ

በበጎች ላይ የሚበቅል ለስላሳና የሚጠቀለል ጸጉር

በፍታ

ከቃጫ ተክል የሚሠራ ክር (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)