am_tn/deu/21/15.md

1.7 KiB

አንዷ የተወደደችና ሌላይቱ የተጠላች

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፣ 1) “ሰውየው ከሚስቶቹ አንደኛዋን ይወዳል፣ ሌላይቱን ሚስቱን ይተላታል” ወይም 2) “ሰውየው ሌላይቱን ሚስቱን ከሚወድበት በበለጠ አንደኛውን ሚስቱን ይወዳታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ሁለቱም ልጆችን ቢወልዱለት

“ሁለቱም ሚስቶቹ ልጆችን ወልደውለታል”

በኩሩ ከተጠላችው ከሆነ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በኩሩ ሰውየው ከሚጠላት ሚስቱ የተወለደ ከሆነ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ከዚያም ሰውየው በ-- ቀን

“ሰውየው በ-- ጊዜ”

ሰውየው ያለውን ልጆቹ እንዲወርሱ ያደርጋል

“ሰውየው ንብረቱን ለልጆቹ ርስት አድርጎ ይሰጣቸዋል”

ከተወደደች ሚስቱ የተወለደውን ልጅ ከተጠላችው ሚስቱ በተወለደው ልጅ ፊት በኩር አያድርገው

“ከተጠላችው ሚስቱ በተወለደው ልጅ ምትክ ከተወዳጅ ሚስቱ የተወለደውን ልጅ በኩር አያድርገው”

ዕጥፍ ድርሻ

“ሁለት ዕጥፍ”

ያ ልጅ የጉብዝናው ጅምሬ ነው

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ያ ልጅ ሰውየው የወንዶች ልጆች አባት መሆኑን የሚያሳይ ነው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)