am_tn/deu/21/13.md

1.4 KiB

የለበሰችውን ልብስ ታውልቀው

ይህንን የምታደርገው በዘዳግም 21፡12 እንደተጠቀሰው ሰውየው ወደ ቤቱ ካመጣትና ጸጉሯን ተቆርጣ፣ የእጅና የእግር ጣት ጥፍሮቿን ከተቆረጠች በኋላ ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የሕዝቧን ልብስ ታወልቅና የእስራኤላውያንን ልብስ ትለብሳለች” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

ተማርካ በተወሰደች ጊዜ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እርሷን በማረክህ ጊዜ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

አንድ ሙሉ ወር

“ወሩን በሙሉ” ወይም “አንድ ወር ሙሉ”

ነገር ግን ባትደሰትባት

ሰውየው ከሴቲቱ ጋር ስለ መተኛቱ ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። አአ.ት፡ “ነገር ግን አብረሃት ከተኛህ በኋላ ሚስትህ እንዳትሆን ከወሰንክ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

ወደፈለገችበት ትሂድ

“መሄድ ወደምትፈልግበት ትሂድ”

አዋርደሃታልና

“ከእርሷ ጋር ከተኛህ በኋላ ስለ ሰደድካት አሳፍረሃታልና”