am_tn/deu/21/08.md

1.2 KiB

የዋጀኸውን

እግዚአብሔር በግብፅ ባሪያ የነበረውን የእስራኤልን ሕዝብ ማዳኑ ሕዝቡን ከባርነት ለመቤዠት ገንዘብ እንደከፈለላቸው በሚመስል መልኩ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በንጹሕ ደም ምክንያት በሕዝብህ በእስራኤል መካከል በደልን አታኑር

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ንጹሕን ሰው እንደ ገደሉ በደለኞች አድርገህ አትቁጠራቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ከዚያም ስለ ፈሰሰው ደም ይቅር ይባላሉ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም ስለ ንጹሑ ሰው ሞት እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ይቅር ይላቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ንጹሕን ደም ከመካከልህ ታስወግዳለህ

“ንጹሕን ሰው ስለ መግደልህ ከእንግዲህ በደለኛ አትሆንም”

በእግዚአብሔር ዐይን ትክክል የሆነውን

x