am_tn/deu/20/19.md

1.4 KiB

ጦርነት ዐውጅ

“በጦርነት ተዋጋ”

በመጥረቢያ ቁረጣቸው

“ዛፎቹን በመጥረቢያ ቁረጣቸው”

ልትከበው በሜዳ ላይ ያለ ዛፍ ሰው ነውን?

ይህ ሰዎቹ አስቀድመው የሚያውቁትን ለማስታወስ የቀረበ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የፍሬ ዛፎች ሰዎች ስላልሆኑ ጠላቶችህ አይደሉም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ለምግብነት የማይውሉ ዛፎች መሆናቸውን ስታውቅ

“የሚበላ ፍሬ የማይሰጡ ዛፎች መሆናቸውን ስታውቅ”

ከበባ ሥራባት

እነዚህ አንድን ከተማ ለመክበብ የሚያስፈልጉ መሰላሎችና ማማዎችን የመሳሰሉ መሣሪያዎችና መዋቅሮች ናቸው።

እስኪወድቅ ድረስ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የከተማይቱ ሰዎች በጦርነቱ እስኪሸነፉ ድረስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ይወድቃል

እዚህ ጋ “እርሱ” የሚወክለው የከተማይቱን ሕዝብ የሚወክለውን ከተማ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)