am_tn/deu/20/10.md

970 B

አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ

እዚህ ጋ “ከተማ” ሕዝቡን ይወክላል። አ.ት፡ “የአንድን ከተማ ሕዝብ ለመውጋት በምትሄድበት ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ለእነዚያ ሰዎች የሰላም ጥሪ አቅርብላቸው

“በከተማው ለሚኖሩ ሰዎች እጅ እንዲሰጡ ዕድል ስጣቸው”

በሮቻቸውን ከከፈቱልህ

እዚህ ጋ “በሮች” የሚያመለክቱት የከተማይቱን በሮች ነው። “በሮቻቸውን ከከፈቱልህ” የሚለው ሐረግ የሚወክለው የሚማረኩትንና እስራኤላውያን ወደ ከተማቸው እንዲገቡ የሚፈቅዱትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “በሰላም ወደ ከተማቸው እንድትገባ ከፈቀዱልህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)