am_tn/deu/20/08.md

1.1 KiB

የሚፈራና ልቡ የሚሸበርበት ሰው ማነው? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ

“እዚህ ያለ የትኛውም ወታደር ቢፈራና ልቡ ቢሸበር ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ”

የሚፈራ ወይም ልቡ የሚሸበርበት

ሁለቱም ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነው። አ.ት፡ “በጦርነት ለመዋጋት የሚፈራ” (See: Doublet)

እንደ ራሱ ልብ የወንድሙም ልብ እንዳይቀልጥ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እርሱ እንደፈራ ሌላውም እስራኤላዊ እንዳይፈራ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የወንድሙ ልብ -- እንደ ራሱ ልብ

እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው የአንድን ሰው ድፍረት ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእነርሱ ላይ አዛዦችን ይሹሙ

“የእስራኤልን ሕዝብ እንዲመሩ አለቆቹ አዛዦችን መሾም አለባቸው”