am_tn/deu/19/17.md

1.6 KiB

ክርክር በመካከላቸው ያለ

“እርስ በእርስ ያልተስማሙ”

በእግዚአብሔር ፊት ይቁሙ፣ በካህናቱና በዳኞቹ ፊት

ይህ ማለት ሁለቱ ሰዎች የእግዚአብሔር ሀልዎት ወደሚያድርበት ቅዱስ ስፍራ መሄድ አለባቸው ማለት ነው። ስለ እግዚአብሔር ሕጋዊ ውሳኔዎችን የመስጠት ሥልጣን ያላቸው ካህናትና ዳኞች በተቀደሰው ስፍራ አሉ። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

በእግዚአብሔር ፊት ይቁሙ፣ በካህናቱና በዳኞቹ ፊት

“ፊት ይቁሙ” የሚለው ሐረግ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህ ማለት ሥልጣን ወዳለው አካል መሄድና እርሱ ስለ ጉዳዩ ሕጋዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ማድረግ ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ዳኞቹ በጥንቃቄ ይመርምሩ

“ዳኞቹ የሆነውን ነገር ለማወቅ ጠንክረው መሥራት አለባቸው”

ከዚያም በወንድሙ ላይ ለማድረግ የተመኘውን በእርሱ ላይ ታደርግበታለህ

“ከዚያም ሐሰተኛውን ምስክር ሌላውን ሰው እንድትቀጣ በፈለገበት መንገድ ትቀጣዋለህ”

ክፉን ከመካከልህ ታስወግዳለህ

ስማዊ ቅጽል የሆነው “ክፉን” እንደ ቅጽል ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ክፉውን ልምምድ ከመካከልህ ታርቃለህ” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)