am_tn/deu/19/11.md

2.5 KiB

ባልንጀራውን

እዚህ ጋ “ባልንጀራ” ማለት በአጠቃላይ ማንኛውም ሰው ማለት ነው።

አድፍጦ ቢጠብቀው

የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እርሱን ለመግደል ተደብቆ ይጠብቀዋል” ወይም “ሊገድለው ያቅዳል” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

በእርሱ ላይ ይነሣል

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ያጠቃዋል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እስኪሞት ድረስ ክፉኛ ቢያቆስለው

“እስኪሞት ድረስ ቢጎዳው” ወይም “ቢገድለው”

ልከው ከዚያ መልሰው ያምጡት

“እንዲያመጡት ሰው ይላኩ፣ እርሱንም ከተከለለበት ከተማ መልሰው ያምጡት”

አሳልፈው ይስጡት

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አሳልፈው ይስጡት” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ኃላፊነት ባለበት ዘመዱ እጅ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው የአንድን ሰው ሥልጣን ነው። አ.ት፡ “ኃላፊነት ላለበት ዘመዱ ሥልጣን” ወይም “ኃላፊነት ላለበት ዘመዱ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኃላፊነት ያለበት ዘመድ

ይህ የተገደለው ሰው ዘመድ ነው። ይህ ዘመድ ገዳዩን ለመቅጣት ኃላፊ ነው።

እንዲሞት

“ገዳዩ እንዲሞት” ወይም “ኃላፊነት ያለበት ዘመድ ገዳዩን እንዲገድለው”

ዐይንህ አይራራለት

እዚህ ጋ “ዐይንህ” የሚወክለው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “ምሕረት አታድርግለት” ወይም “አትዘንለት” (See: Synecdoche)

የደምን በደል ከእስራኤል አስወግድ

እዚህ ጋ “የደም በደል” የሚወክለው ንጹሕ የሆነውን ሰው የመግደልን በደል ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ በንጹሕ ሰው ሞት ምክንያት በደለኛ እንዳይሆን ነፍሰ ገዳዩን ግደለው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእስራኤል

እዚህ ጋ “እስራኤል” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)