am_tn/deu/19/08.md

3.6 KiB

ድንበርህን ያሰፋል

“የምትወርሰውን ተጨማሪ መሬት ይሰጥሃል”

ለቅድም አያቶችህ እንደማለው

“እርሱ እንደሚያደርገው ለቅድም አያቶችህ ተስፋ የሰጠውን”

ታደርጋቸው ዘንድ እነዚህን ትዕዛዛት በሙሉ ብትጠብቅ

“እነዚህን ትዕዛዛት በሙሉ ብትታዘዝ”

ዘወትር በመንገዶቹ እንድትሄድ

እግዚአብሔር፣ አንድ ሰው እንዲኖረውና እንዲያደርገው የሚፈልግበት አግባብ እንደ እግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና ተቆጥሮ ተነግሯል። እግዚአብሔርን የሚታዘዝ ሰው በእግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና እንደ ሄደ ተቆጥሮ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ዘወትር እንድትታዘዘው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከዚያም ሦስት ተጨማሪ ከተሞችን ለራስህ ትጨምራለህ

የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም አንድ ሰው በድንገት ሌላውን ሰው ከገደለ እንዲያመልጥበት ተጨማሪ ሦስት ከተሞችን ትመርጣለህ” (ቁጥሮች እና Assumed Knowl- edge and Implicit Information የሚለውን ተመልከት)

ከእነዚህ ከሦስቱ በተጨማሪ

“አስቀድሞ ካዘጋጀኻቸው ከሦስቱ ከተሞች በተጨማሪ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)

ንጹሕ ደም እንዳይፈስ ይህንን አድርግ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የቤተሰቡ አባላት ንጹሕ የሆነውን ሰው እንዳይገድሉ ይህንን አድርግ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ንጹሕ ደም እንዳይፈስ

እዚህ ጋ “ደም” የሚወክለው የሰውን ሕይወት ነው። ደም ማፍሰስ ማለት ሰው መግደል ማለት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ንጹሕ የሆነውን ሰው አይግደል” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በምድሪቱ መካከል

“በምድሪቱ” ወይም “በግዛቱ”

አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ

እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ የሚሰጣቸው ምድር ርስት እንደሆነ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የደም በደለኛ እንዳትሆን

የእስራኤል ሕዝብ “ከደም ተበቃዩ” የሚያመልጥበትን ከተማ ባለመሥራታቸው በሚሞተው ሰው ምክንያት በደለኛ መሆናቸው የሟቹ በደል በእነርሱ ላይ እንደሚሆን ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የደም በደል

እዚህ ጋ “ደም” የሚወክለው ሕይወትን ሲሆን “የደም በደለኛ” የሚያመለክተው አንድ ሰው ንጹሕ የሆነን ሰው ስለ መግደሉ የሚኖርበትን በደል ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በአንተ ላይ እንዳይሆን

ይህ ማለት አንድ የቤተሰብ አባል ንጽሕ የሆነን ሰው ቢገድል፣ ከዚያም ይህ እንዲሆን ዝም በማለታቸው የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ በደለኛ ይሆናሉ።