am_tn/deu/19/06.md

1.2 KiB

ደም ተበቃዩ

እዚህ ጋ “ደም” የሚወክለው የተገደለውን ሰው ነው። “ደም ተበቃዩ” ሰው የሟቹ የቅርብ ዘመድ ነው። ገዳዩን ለመቅጣት ኃላፊነቱ የዚህ ዘመድ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሕይወትን የሚያጠፋ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ሌላውን ሰው የገደለ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በንዴት ግሎ

የአንድ ሰው በጣም መቆጣት ልክ ቁጣ እንደሚግል አንዳች ነገር ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “በጣም ተቆጥቶ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይመታውና ይገድለዋል

"ደም ተበቃዩ ሟችን የገደለውን ሰው ይመታና ይገድለዋል”

አስቀድሞ ባልንጀራውን አልጠላውምና ያ ሰው መሞት የሚገባው ባይሆንም

“ሌላውን ሰው የገደለው በድንገት ስለሆነና ጠላቱ ስላልነበረ፣ ሰውየውን ለመጉዳትም ስላላቀደ ያ ሰው መሞት የሚገባው ባይሆንም”