2.2 KiB
ሕጉ ይህ ነው
“መመሪያዎቹ እነዚህ ናቸው” ወይም “አቅጣጫዎቹ እነዚህ ናቸው”
ሌላውን የገደለ
“ሰው” የሚለው ቃል እንዳለበት ይታወቃል። አ.ት፡ “ሌላውን ሰው የገደለ ሰው” (See: Ellipsis)
ወደዚያ የሚሸሽ
“ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ የሚያመልጥ” ወይም “ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ የሚሮጥ”
ለመኖር
“ሕይወቱን ለማዳን”። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የሟች ቤተሰብ ተበቅለው እንዳይገድሉት” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ማንም ሳያውቅ ባልንጀራውን የሚገድል
እዚህ ጋ “ባልንጀራ” ማለት በአጠቃላይ የትኛውም ሰው ማለት ነው። አ.ት፡ “በድንገት ሌላውን ሰው የሚገድል የትኛውም ሰው”
አስቀድሞ ጥላቻ ሳይኖረው
“ነገር ግን ባልንጀራውን ከመግደሉ በፊት አልጠላው እንደሆነ”። ባልንጀራውን አስቦበት የሚገድልበት ምክንያት እንዳልነበረው ያመለክታል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ
ደራሲው አንድ ሰው ሌላውን በድንገት የሚገድልበትን መላ ምታዊ ሁኔታ ይሰጣል። (See: Hypothetical Situations)
ብረቱ ከእጀታው ወልቆ
የመጥረቢያው የብረት ክፍል ከእንጨቱ እጀታ ወልቆ
ባልንጀራውን መትቶ ቢገድለው
ይህ ማለት የመጥረቢያው ራስ ባልንጀራውን መትቶ ገድሎታል ማለት ነው።
ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ -- ሕይወቱን ያድን
የሟቹ ሰው ቤተሰብ ምናልባት ሊበቀሉት እንደሚሞክሩ ያመለክታል። በዚያ ያሉት ሰዎች ጥበቃ እንዲያደርጉለት እርሱን የገደለው ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ መሸሽ ይችላል (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)