1.4 KiB
1.4 KiB
በትዕቢት ቃልን የሚናገር
“መልዕክት ለመናገር የሚደፍር” ወይም “በዕብሪተኝነት መልዕክት የሚናገር”
በስሜ
እዚህ ጋ “ስሜ” የሚያመለክተው ራሱን እግዚአብሔርንና ሥልጣኑን ነው። አ.ት፡ “ለእኔ” ወይም “በእኔ ሥልጣን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ቃልን
“መልዕክትን”
በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር
እዚህ ጋ “ስም” የሚወክለው አማልክቱን ራሳቸውን ወይም ሥልጣናቸውን ነው። ይህ ማለት ሐሰተኞቹ አማልክት አንድን መልዕክት እንዲናገር እንደ ነገሩት ነቢዩ ያስታውቃል ማለት ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በልብህ እንዲህ ትላለህ
እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው የሰውን አሳብ ነው። አ.ት፡ “ራስህን ትጠይቃለህ” ወይም “ለራስህ ትናገራለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
መልዕክቱን እግዚአብሔር እንዳልተናገረ እንዴት እንለያለን?
“ነቢዩ የሚናገረው መልዕክት ከእግዚአብሔር መሆኑን እንዴት እናውቃለን? እዚህ ጋ “እኛ” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው።