am_tn/deu/18/15.md

2.1 KiB

አምላክህ እግዚአብሔር ነቢይ ያስነሣልሃል

ነቢይ እንዲሆን እግዚአብሔር አንድን ሰው መሾሙ እግዚአብሔር ሰውየውን እንደሚያነሣው ወይም ብድግ እንደሚያደርገው ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከወንድሞችህ አንዱ

“እንዳንተው እስራኤላዊ ከሆኑት አንዱ”

የጠየቅኸው ይህንን ነው

እዚህ ጋ “አንተ” የሚያመለክተው ከ40 ዓመታት በፊት በኮሬብ ተራራ የነበሩትን እስራኤላውያንን ነው።

በኮሬብ ጉባዔ በተደረገበት ቀን

“በኮሬብ በአንድ ላይ በተሰበሰባችሁበት ቀን”

ጉባዔ በተደረገበት ቀን፣ ‘የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ አንስማ፣ ይህንን ታላቅ እሳትም ከእንግዲህ አንይ፣ እንዲህ ካልሆነ እንሞታለን’ ስትል

ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛ የሆነው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ጉባዔ በተደረገበት ቀን እንዳትሞት ፈርተህ ስለነበር የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማትም ሆነ ከእንግዲህ የእርሱን ታላቅ እሳት ማየት እንደማትፈልግ በተናገርክ ጊዜ” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)

የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደገና አንስማ

እዚህ ጋ እግዚአብሔር ለተናገረው አጽንዖት ለመስጠት የእርሱ በሆነ ”ድምፅ” ተወክሏል። አ.ት፡ “አምላካችን እግዚአብሔር እንደገና ሲናገር አንስማ” (See: Synecdoche)