am_tn/deu/18/09.md

1.7 KiB

በምትመጣበት ጊዜ

(ሂድ እና ና የሚለውን ተመልከት)

የእነዚያን ሕዝቦች አስጸያፊ ተግባር ለመጠበቅ አትማር

በዙሪያቸው ያሉትን ሀገራት ሰዎች ሃይማኖታዊ ተግባራት እግዚአብሔር ይጠላል። እርሱ እጅግ ክፉዎች እንደሆኑ አድርጎ ይመለክታቸዋል። እዚህ ጋ “ሀገሮች” ሰዎቹን ይወክላሉ። አ.ት፡ “የሌሎች ሀገራት ሰዎች የሚያደርጓቸውን አስከፊ ነገሮች አታድርጉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመካከልህ ማንም አይገኝ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በመካከልህ ማንም አይኑር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ማንም የሚጠነቁል -- ከመናፍስት ጋር የሚነጋገር

እነዚህ አስማትን የሚለማመዱ የተለዩ ሰዎች ናቸው። የትኛውንም ዓይነት አስማት እግዚአብሔር ከልክሏል። ለእንደዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች ሁሉ የሚሆን ቃል ከሌለህ በይበልጥ ጥቅል በሆነ መልኩ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወደፊት የሚሆነውን ለማወቅ በመሞከር፣ ዕጣ ለመጣል ወይም የሙታንን መናፍስት ለማነጋገር አስማት የሚጠቀም ማንም ቢሆን”

በሲኒ የሚገኙ ምልክቶችን የሚያነብ

በሲኒ ውስጥ ያሉ ቅርጾችንና ስዕሎችን የሚያነብና ከሚያየው ተነሥቶ ወደፊት የሚሆኑትን ሁነቶች የሚተነብይ