am_tn/deu/17/20.md

1.1 KiB

ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይታበይ

እዚህ ጋ “ልቡ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። የአንድ ንጉሥ ዕብሪተኛ መሆን ልቡ እንደ ታበየ ሆኖ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ዕብሪተኛ እንዳይሆን” ወይም “እንደ እርሱ ካለው እስራኤላዊ ይልቅ የተሻለ እንደሆነ እንዳያስብ” (Synecdoche እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከትዕዛዛቱ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ እንዳይመለስ

አንድ ንጉሥ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት አለመታዘዙ አንድ ሰው ከትክክለኛው መንገድ እንደሚወጣ በሚመስል መልኩ ተነግሯል። ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከትዕዛዛቱ የትኛውንም ሳይታዘዝ እንዳይቀር” ወይም “ትዕዛዛቱን ሁሉ እንዲጠብቅ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ምጸት የሚለውን ተመልከት)