am_tn/deu/17/18.md

1.1 KiB

በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ

እዚህ ጋ “ዙፋን” የሚወክለው ሰውየው እንደ ንጉሥ የሚኖረውን ኃይልና ሥልጣን ነው። በዙፋን መቀመጥ ንጉሥ መሆን ማለት ነው። አ.ት፡ “ንጉሥ በሚሆንበት ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የዚህን ሕግ ቅጅ ለራሱ በጥቅልል ላይ ይጻፈው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “በግሉ የዚህን ሕግ ቅጅ በጥቅልል ላይ ለራሱ ይጻፍ” ወይም 2) “የዚህን ሕግ ቅጅ የሚጽፍለትን ሰው ይሹም”

ሌዋውያን በሆኑት ካህናት ፊት ካለው ሕግ

“ሌዋውያን ካህናት ከሚጠብቁት ከሕጉ ቅጅ”

የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ እና እነዚህን ሥርዓቶች እንዲጠብቅ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ሲሆን ንጉሡ የእግዚአብሔርን ሕግ በሙሉ መታዘዝ እንዳለበት አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Parallelism)