am_tn/deu/17/14.md

2.6 KiB

ወደ ምድሪቱ በምትመጡበት ጊዜ

“በምትመጡበት” የሚለው ቃል “በምትሄዱበት” ወይም “ስትገቡ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። (ሂድ እና ና የሚለውን ተመልከት)

‘በዙሪያዬ እንዳሉት ሕዝቦች በራሴ ላይ ንጉሥ አነግሣለሁ’ በምትልበት ጊዜ፣ ያን ጊዜ

ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛ የሆነው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም በዙሪያህ ያሉ ሀገራት ሕዝቦች ንጉሥ እንዳላቸው አንተም እንዲኖርህ ትወስናለህ፣ ከዚያም” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)

በዙሪያዬ እንዳሉት -- በራሴ ላይ ንጉሥ አነግሣለሁ

ሙሴ እንደ አንድ ሰው ቆጥሮ የሚናገራቸው ሰዎች አሉት። ወደ ብዙ ቁጥር ተውላጠ ስም መተርጎም በይበልጥ የተለመደ ይሆናል። አ.ት፡ “በዙሪያችን … ለራሳችን እናነግሣለን” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)

ለራሴ ንጉሥ አነግሣለሁ

በእስራኤል ለአንድ ሰው እንደ ንጉሥ እንዲገዛቸው ሥልጣን መስጠታቸው ሕዝቡ ያንን ሰው ከእነርሱ በላይ ባለ ቦታ ላይ እንዳስቀመጡት ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በዙሪያዬ እንዳሉት ሕዝቦች ሁሉ

“በዙሪያዬ ያሉ ሕዝቦች”

ሀገራት ሁሉ

እዚህ ጋ “ሀገራት” የሚወክሉት በሀገራቱ ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከወንድሞችህ መካከል አንዱን

“እንደ አንተው እስራኤላዊ ከሆኑት አንዱን”

በራስህ ላይ ወንድምህ ያልሆነውን መጻተኛ

የእነዚህ ሁለት ሐረጎች ትርጉም ተመሳሳይ ነው። ሁለቱም የሚያመለክቱት እስራኤላዊ ያልሆነውን ሰው ነው። የእስራኤል ሕዝብ መጻተኛው እንዲገዛቸው እንዳይፈቅዱ እግዚአብሔር አጽንዖት ሰጥቷል። አ.ት፡ “በራስህ ላይ መጻተኛውን” ወይም “እስራኤላዊ ያልሆነውን በራስህ ላይ” (See: Doublet)