am_tn/deu/17/05.md

1.5 KiB

ሞት የሚገባው ሰው በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ይገደል

እዚህ ጋ “አፍ” የሚወክለው የመስካሪዎችን ምስክርነት ነው። ይህ ወደ አድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በሰውየው ላይ ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ከመሰከሩበት ከዚያ በኋላ ታስወግደዋለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር፣ አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)

ነገር ግን በአንድ ምስክር አፍ ብቻ መገደል የለበትም

እዚህ ጋ “አፍ” የሚወክለው የመስካሪውን ምስክርነት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ነገር ግን በእርሱ ላይ የሚመሰክረው አንድ ሰው ብቻ ከሆነ ያንን ሰው ማስወገድ አይኖርብህም” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ፣ ከዚያም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ምስክሮችን በሙሉ ነው። አ.ት፡ “ድንጋዮቹን ለመወርወር ምስክሮቹ ራሳቸው የመጀመሪያ ይሁኑ፣ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በእርሱ ላይ ድንጋይ በመወርወር ይግደሉት” (See: Synecdoche)