am_tn/deu/17/02.md

2.0 KiB

ቢገኝ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ብታገኝ” ወይም “አንድ ሰው ቢኖር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በየትኛውም የከተማህ በሮች ውስጥ

እዚህ ጋ “የከተማ በሮች” ከተሞችን ወይም መንደሮችን ይወክላሉ። አ.ት፡ “ከከተሞችህ በአንዱ ቢኖር” (See: Synecdoche)

በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን

የእግዚአብሔር ፊት የእግዚአብሔርን ውሳኔ ወይም ምዘና ይወክላል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ክፉ ነው ብሎ የሚያስበው ነገር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቃል ኪዳኑን ይተላለፋል

“ቃል ኪዳኑን አይታዘዝም”

የትኛውንም የሰማይ ሰራዊት

“የትኛውንም ኮከብ”

እኔ ያላዘዝኩትን

“እንዲያደርገው ለማንም ያላዘዝኩትን”

ስለዚህ ነገር ቢነገርህ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ስለዚህ የእምቢተኝነት ተግባር ቢነግርህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በጥንቃቄ መርምር

የነገር ስም የሆነው “ምርመራ” እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሆነውን ነገር በጥንቃቄ መርምር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

እንዲህ ያለ አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ተደርጎ እንደሆን

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው እንዲህ ያለውን አስከፊ ነገር በእስራኤል አድርጎ እንደሆነ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)