am_tn/deu/16/18.md

3.4 KiB

ዳኞችን አድርግ

“ዳኞችን ሹም” ወይም “ዳኞችን ምረጥ”

በከተሞችህ በሮች ውስጥ

እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክለው ከተማን ወይም መንደርን ነው። አ.ት፡ “በመንደሮችህ ሁሉ ውስጥ” (See: Synecdoche)

ይወሰዳሉ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ትመርጣቸዋለህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በሕዝቡ ላይ በጽድቅ ፍርድ ዳኙ

“ሕዝቡን በፍትሐዊነት ዳኙ”

ፍትሕን በኃይል ምክንያት አታዛባ

ሙሴ ስለ ፍትሕ ሲናገር ብርቱው ሰው ከደካማው ሰው በጉልበት እንደሚቀማው አንዳች ቁሳዊ አካል አድርጎ ይናገራል። ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊነገር ይችላል። የአንተ ቋንቋ “ለመውሰድ ኃይል ተጠቀም” ለማለት አንድ ቃል ይኖረው ይሆናል። አ.ት፡ “በምትዳኝበት ጊዜ ኢፍትሐዊ አትሁን” ወይም “ትክክለኛ ውሳኔዎችን ስጥ” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት and Double Negatives))

አታድርግ

እዚህ ጋ “አንተ” የሚያመለክተው እነዚያን ዳኞችና አለቆች ተደርገው የተሾሙትን ነው። (See: Forms of You)

ጉቦ የጠቢቡን ዓይኖች ያሳውራልና የጻድቁንም ቃል ያጣምማልና

ጉቦ መቀበል ሰዎችን እንደሚያበላቸው ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ጉቦን የሚቀበል ጥበበኛ ሰው እንኳን ይታወራል፣ ጉቦን የሚቀበል ጻድቅ ሰውም እንኳን ሐሰትን ይናገራል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጉቦ የጠቢቡን ዓይኖች ያሳውራል

ክፉ በሆነው ነገር ላይ እንዳይናገር ጉቦን የሚቀበል ጠቢብ ሰው የሚታወር ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጠቢቡ

“ጠቢቡ” የሚለው ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ጠቢብ ሰው” ወይም “ጥበበኛ ሰዎች” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)

የጻድቁን ቃል ያጣምማል

“ጻድቅ” የሚለው ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ጻድቁን ሰው እንዲዋሽ ያደርገዋል” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)

ፍትሕን ተከተል፣ ፍትሕን ብቻ ተከተል

ፍትሕ በሚራመድ ሰው ተመስሎ ተነግሮለታል። ትክክለኛና ቅን የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው ፍትሕን በቅርበት እንደተከተለ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “አግባብነት ያለውን ብቻ አድርግ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር ውረስ

እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚሰጣቸውን ምድር መቀበል ሕዝቡ ምድሪቱን ከእግዚአብሔር እንደሚወርስ ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)