am_tn/deu/15/11.md

1.8 KiB

ድኻ ከምድር ላይ አይጠፋምና

ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በምድር ላይ ድኾች ሁሌም ይኖራሉና” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)

ድኾች

“ድኾች” የሚለው ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሆኖ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ድኾች ሰዎች” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)

‘በምድርህ ላይ -- እጅህን መክፈት አለብህ’ ብዬ አዝሃለሁ

ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በምድርህ ላይ -- እጅህን እንድትከፍት አዝሃለሁ” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ)

ለወንድምህ፣ ለችግረኛና ለድኻው እጅህን ክፍት

አንድን ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ የሚሆን ሰው እጁን እንደሚከፍት ተደርጎ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “እስራኤላዊ ጓደኛህን፣ የተቸገሩትንና ድኾችን እርዳቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ለወንድምህ፣ ለችግረኛና ለድኻው

“ችግረኛ” እና “ድኻ” የሚሉት ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ሆኖ እነዚህ ራሳቸውን መርዳት የማችሉ ሰዎች መሆናቸው ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ራሳቸውን መርዳት የማይችሉ እስራኤላውያን ጓደኞችህን እርዳቸው” (See: Doublet)