am_tn/deu/15/09.md

2.0 KiB

የሚል ክፉ አሳብ በልብህ አይኑር

እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው የሰውን አዕምሮ ነው። አ.ት፡ “ክፍ አሳብ አታስብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሰባተኛው ዓመት፣ የምሕረት ዓመት ቀርቧል

ይህ የምሕረት ዓመት ስለቀረበ ይህንን የሚያስበው ሰው ድኻው ሰው ሊመልስለት እንደማይችል በማሰብ ድኻውን ለመርዳት እንደሚያመነታ ያመለክታል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

ሰባተኛው ዓመት

“ሰባተኛው” የሚለው ቃል የሰባት ደረጃ አመልካች ቁጥር ነው። (ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)

የምሕረት ዓመት

“ዕዳን የመሰረዝ ዓመት”

ቀርቧል

በቅርብ የሚሆን አንድ ነገር በአካል የቀረበ በሚመስል መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “በቅርቡ ይሆናል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስስታም ሆነህ ለድኻው ወንድምህ ሳትሰጠው እንዳትቀር

“አትጨክን፣ ለእስራኤላዊ ጓደኛህ የትኛውንም ነገር ከመስጠት አትንፈገው”

ወደ እግዚአብሔር ያለቅሳል

“ዕርዳታ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል”

ኃጢአት ይሆንብሃል

“አንተ ያደረግኸውን እግዚአብሔር ኃጢአት ይለዋል”

ልብህን አይጸጽተው

እዚህ ጋ “ልብ” ሙሉውን ሰው ይወክላል። አ.ት፡ “ቅር አይበልህ” ወይም “ደስ ይበልህ” (Synecdoche እና ምጸት የሚለውን ተመልከት)

እጅህን በምታኖርበት ሁሉ

እዚህ ጋ “እጅህን በምታኖርበት” የሚወክለው ሙሉውን ሰውና እርሱ የሚሠራውን ሥራ ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ሁሉ” (See: Synecdoche)