am_tn/deu/13/17.md

2.1 KiB

ለመጥፋት ከተለዩ ከእነዚያ ነገሮች አንዱም እጅህ ላይ አይጣበቅ

እግዚአብሔር አንድን ነገር መርገሙና ሊያጠፋው መማሉ እርሱ ቁሱን ከሌሎች ነገሮች ለይቶ እንደሚያስቀምጠው ሆኖ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አጥፋው ብሎ ካዘዘህ ነገር ውስጥ የትኛውንም ማቆየት የለብህም” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

እጅህ ላይ አይጣበቅ

ይህ አንድ ሰው የሆነ ነገርን ለራሱ የሚያቆይበት መንገድ ነው። አ.ት፡ “አታቆይ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ከቁጣው መዓት ይመለሳል

እግዚአብሔር ከእንግዲህ ያለመቆጣቱ ቁጣው እንደ አንድ ቁስ ተቆጥሮ እግዚአብሔር በአካል ከእርሱ እንደሚመለስ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር መቆጣቱን ይተዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ለአባቶችህ

እዚህ ጋ “አባቶችህ” ማለት አያቶችህ ወይም ቅድም አያቶችህ ማለት ነው።

የእግዚአብሔርን ድምፅ ሰምተሃል

እዚህ ጋ “ድምፅ” እግዚአብሔር የሚናገረውን ይወክላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የሚናገረውን ታዘሃል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በአምላክህ በእግዚአብሔር ዐይን ትክክል የሆነውን

ዐይን ማየትን ይወክላል፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ውሳኔ ትክክል የሆነውን” ወይም “አምላክህ እግዚአብሔር ትክክል እንደሆነ የሚቆጥረውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)