am_tn/deu/13/12.md

1.7 KiB

አንዳንድ ክፉ ሰዎች ከመካከልህ ሄደው

“ከመካከልህ” የሚለው ሐረግ እነዚህ ክፉ ሰዎች በማኅበረሰቡ መካከል የሚኖሩ እስራኤላውያን ነበሩ ማለት ነው።

የከተማቸውን ነዋሪዎች ሰብስበው፣ ‘ሄደን የማታውቋቸውን አማልክት እናምልክ’ ቢሉ

ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የማያውቋቸውን አማልክት ሄደው እንዲያመልኩ በከተማቸው የሚኖሩትን አስገድደዋል”። (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)

የከተማቸውን ነዋሪዎች ሰብስበው

አንድ ሰው ሌላውን እግዚአብሔርን እንዳይታዘዝ ቢያደርገው ያ ሰው በአካሉ ከእግዚአብሔር ተለይቶ እንዲመለስ እንዳደረገው ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መረጃውን አጣራ፣ ፈትሽ፣ በሚገባ መርምር

እነዚህ ሐረጎች ሁሉ በመሠረቱ የሚሉት አንድ ነገር ነው። ሙሴ በከተማይቱ ስለሆነው ነገር እውነቱን በጥንቃቄ እንዲያጣሩ አጽንዖት እየሰጠ ነው። (See: Doublet)

እንዲህ ያለ አስጸያፊ ነገር በመካከላችሁ ተደርጎ እንደሆን

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የከተማይቱ ሰዎች እንዲህ ያለ አስከፊ ነገር አድርገው እንደሆን (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)