am_tn/deu/13/06.md

1.7 KiB

በእቅፍህ ያለች ሚስትህ

እቅፍ የሰው ድረት ነው። ይህ የአነጋገር ዘይቤ ወደ ደረቱ አስጠግቶ ይይዛታል፣ ይኸውም ይወዳታል፣ ይንከባከባታል ማለት ነው። አ.ት፡ “የምትወዳት ሚስትህ” ወይም “በፍቅር የምታቅፋት ሚስትህ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እንደ ነፍስህ የሆነ ጓደኛህ

እዚህ ጋ “ነፍስ” የሚወክለው የሰውን ሕይወት ነው። ይህ ማለት ሰውየው ለራሱ ሕይወት የሚገደውን ያህል ስለ ጓደኛው ይገደዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ውድ ጓደኛህ” ወይም “ራስህን የምትወደውን ያህል የምትወደው ጓደኛህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በምስጢር ሊያስትህ፣ ‘በሌላው የምድር ጫፍ -- እንሂድና እናምልክ’ ቢልህ

ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ወደ ሌላው የምድር ጫፍ ሄደህ እንድታመልክ ሊያሳምንህ በምስጢር ይሞክራል” (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)

በክበብህ ያሉ

“በዙሪያህ ያሉ”

ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ

እዚህ ጋ ሁለቱ የምድር ጽንፍ ማጣቀሻዎች “በምድር ላይ በሁሉ ስፍራ” ማለት ነው። አ.ት፡ “በመላው ምድር ላይ” (See: Merism)