am_tn/deu/13/04.md

3.4 KiB

አምላካችሁን እግዚአብሔርን ተከተሉት

እግዚአብሔርን መታዘዝና ማምለክ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ኋላ እንደ ሄዱ ወይም እንደተከተሉት ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ታዘዙ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ድምፁን ታዘዙ

እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚወክለው እግዚአብሔር የሚናገረውን ነው። አ.ት፡ “እርሱ የሚለውን ታዘዙ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእርሱ ጋር ተጣበቁ

ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት መኖሩና ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መታመን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚጣበቅ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “በእርሱ ተማመን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይገደል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “መግደል አለብህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

አመፅን ተናግሯልና

የነገር ስም የሆነው “አመፅ” እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እንድታምፅ ሊያደርግህ ሞክሯል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ከባርነት ቤት የተቤዠህን

እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ባሪያ ከነበሩበት ከግብፅ ማዳኑ ሕዝቡን ከባርነት ለመቤዠት ገንዘብ እንደከፈለ በሚመስል መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “ ባሪያዎች ከነበራችሁበት ስፍራ ያዳናችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የባርነት ቤት

እዚህ ጋ “የባርነት ቤት” የእግዚአብሔር ሕዝብ ባሪያዎች የነበሩበትን ግብፅን ይወክላል። አ.ት፡ “ባሪያዎች የነበራችሁበት ግብፅ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አምላካችሁ እግዚአብሔር እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትወጡ

እግዚአብሔር አንድ ሰው እንዴት መኖር ወይም ማድረግ እንዳለበት የሚፈልግበት ሁኔታ ሕዝቡ እንዲሄዱበት እንደሚፈልገው መንገድ ወይም ጎዳና ሆኖ ተነግሯል። አንድን ሰው እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ለማስቆም የሚሞክር በእግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና ላይ እንዳይሄድ እንደተከላከል ሆኖ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘውን እንዳትፈጽም የሚያደርግህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስለዚህ ክፋትን ከመካከላችሁ አርቁ

እዚህ ጋ “ክፋትን” የሚያመለክተው ክፉ ሰውን ወይም ክፉ ባህርይን ነው። ይህ ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለዚህ ይህንን ክፉ ነገር የሚያደርገውን ሰው ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ማስወገድ አለብህ” ወይም “ስለዚህ ይህንን ክፉ ሰው መግደል አለብህ” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)