am_tn/deu/13/01.md

2.4 KiB

በመካከላችሁ ቢነሣ

“በመካከላችሁ ቢመጣ” ወይም “በመካከላችሁ ነኝ ቢል”

የሕልመኛው ሕልሞች

ይህ ከእግዚአብሔር በሕልም መልዕክት የሚቀበል ሰው ነው።

ምልክትን ወይም ድንቅን

እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ የተለያዩ ተአምራቶችን ያመለክታል። (See: Doublet)

ቢሆን

“ቢከናወን” ወይም “ቢመጣ”

ቢነግርሃና፣ ‘ሌሎች አማልክትን እንከተል፣ የማታውቃቸውን እናምልክ’ ቢልህ አትስማው

ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንድታመልክና እንድታገለግል ቢነግርህ አትስማው” (ቀጥተና እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)

ከሌሎች አማልክት ኋላ እንሂድ

ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከሌሎች አማልክት ኋላ መሄድ ወይም መከተል ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን እንከተል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከማታውቃቸው ሌሎች አማልክት ኋላ ሂድ

“ከማታውቃቸው አማልክት” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ሌሎች የሕዝብ ወገኖች የሚያመልኳቸውን አማልክት ነው። ራሱን ስለገለጠላቸውና ኃይሉን ስለተለማመዱት እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ያውቁታል።

የዚያን ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቃል አትስማ

“ያ ነቢይ የሚለውንም ሆነ ሕልም አላሚው የሚናገረውን አትስማው”

በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ

እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። እነዚህ ሁለት ሐረጎች “በፍጹም” ወይም “በቅንነት” የሚል ትርጉም እንዲሰጡ በአንድነት ጥቅም ላይ ውለዋል። ይህንን በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)