am_tn/deu/12/29.md

2.7 KiB

ሕዝቦችን ይቆርጣቸዋል

እግዚአብሔር በከነዓን የሚኖሩትን የሕዝብ ወገኖች ማጥፋቱ አንድ ሰው ቁራጭ ጨርቅ ወይም ከዛፍ ላይ ቅርንጫፍን እንደሚቆርጥ እንደሚቆርጣቸው ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሕዝቦች

እዚህ ጋ “ሕዝቦች” የሚወክሉት በከነዓን የሚኖሩትን ሰዎች ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ታስወጧቸዋላችሁ፣ በምታስወጧቸው ጊዜ

“ሁሉንም ነገር በምትወስዱባቸው ጊዜ”

ለራሳችሁ ትኩረት ስጡ

“ተጠንቀቁ”

እነርሱን በመከተል እንዳትጠመዱ -- አማልክታቸውን ለመጠየቅ በመሞከር እንዳትጠመዱ

ስለ ሌሎች አማልክት የሚማርና የሚያመልክ ሰው በአዳኝ ወጥመድ እንደሚያዝ ሆኖ ተነግሮለታል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እንደ እነርሱ አታድርጉ … አማልክታቸውን የመጠየቅ ሙከራ ለማድረግ እንዳትማሩ” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት))

እነርሱን በመከተል አትጠመዱ

የከነዓን የሕዝብ ወገኖች ጣዖታትን እንደሚያመልኩ እስራኤላውያን ጣዖታትን ማምለካቸው ከሌሎች የሕዝብ ወገኖች በስተኋላ እንደ ተከተሉ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእናንተ አስቀድሞ ከጠፉ በኋላ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በፊታችሁ ካጠፋቸው በኋላ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

‘እነዚህ ሕዝቦች አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እኔም እንደዚያው አደርጋለሁ’ ብለህ ብትጠይቅ

ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛ የሆነው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንተም እንደዚያው ልታደርግ እነዚያ የሕዝብ ወገኖች አማልክታቸውን እንዴት እንዳመለኩ ብትጠይቅ” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)