1.3 KiB
1.3 KiB
እኔ የማዝህን እነዚህን ቃላት በሙሉ ስማ፣ በጥንቃቄም ጠብቃቸው
“የማዝህን ሁሉ በጥንቃቄ ስማና ታዘዘው”
ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንልህ
እዚህ ጋ “ልጆች” ማለት ተወላጆቻቸው ሁሉ ማለት ነው። አ.ት፡ “አንተና ተወላጆችህ እንድትበለጽጉ” (See: Synecdoche)
መልካምና ትክክለኛውን ነገር በምታደርግበት ጊዜ
“መልካም” እና “ትክክለኛ” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ትክክለኛ ባህርይ አስፈላጊ በመሆኑ ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ትክክል የሆነውን በምታደርግበት ጊዜ” (See: Doublet)
በእግዚአብሔር ዐይን መልካምና ትክክል
ዐይን ማየትን ይወክላል፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ውሳኔ መልካምና ትክክል የሆነው” ወይም “እግዚአብሔር መልካምና ትክክል ነው የሚለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)