am_tn/deu/12/23.md

1.2 KiB

ደሙ ሕይወቱ ነው

እዚህ ጋ ደም ሕይወትን የሚያቆይበት መንገድ ደም ራሱ ሕይወት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ደሙ ሕይወትን ያቆያል” ወይም “ሰዎችና እንስሳት በሕይወት እንዲኖሩ የሚያደርጋቸው ደም ነው።” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሕይወቱን ከሥጋው ጋር አትብላው

እዚህ ጋ፣ “ሕይወት” የሚለው ቃል የሚወክለው ሕይወትን የሚያቆየውን ደሙን ነው። አ.ት፡ “ሕይወትን የሚያቆየውን ከሥጋ ጋር አትብላው” ወይም “ሕይወትን የሚያቆየውን ደም ከሥጋ ጋር አትብላ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእግዚአብሔር ዐይን ትክክል የሆነውን

ዐይን ማየትን ይወክላል፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ውሳኔ ትክክል የሆነው” ወይም “እግዚአብሔር ትክክል ነው የሚለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)