am_tn/deu/12/15.md

1.8 KiB

ይሁን እንጂ፣ በየበሮቻችሁ ውስጥ እንስሶችን አርዳችሁ መብላት ትችላላችሁ

ሕዝቡ ለመሥዋዕት እንስሶችን ማረድ የሚችለው እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ብቻ ነው። ለምግብ የሚሆኑ እንስሶችን በፈለጉበት ሁሉ ማረድ ይችላሉ። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information

በየበሮቻችሁ ውስጥ

እዚህ ጋ “በሮች” ከተማውን በሙሉ ይወክላሉ። አ.ት፡ “በከተማችሁ ውስጥ” ወይም “በቤታችሁ” (See: Synecdoche)

ንጹሕ ያልሆኑ ሰዎች

ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀባይነት የሌለው ሰው በአካሉ ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ንጹሕ የሆኑ ሰዎች

ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀባይነት ያለው ሰው በአካሉ ንጹሕ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሚዳቋና ድኩላ

እነዚህ በፍጥነት መሮጥ የሚያስችል ቀጭንና ረጅም እግሮች ያሏቸው የዱር እንስሶች ናቸው። አ.ት፡ “አጋዘንና ድኩላ” (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)

ነገር ግን ደሙን አትብሉ

ደም ሕይወትን ስለሚወክል ሕዝቡ ደሙን ከምግባቸው ጋር እንዲበሉት እግዚአብሔር አልፈቀደላቸውም። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)