am_tn/deu/12/10.md

1.4 KiB

በምድሪቱ ስትኖሩ

ይህ የሚያመለክተው የከነዓንን ምድር ነው።

አማላካችሁ እግዚአብሔር እንድትወርሷት በሚያደርጋችሁ ምድር ላይ

እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር ለእስራኤል ሕዝብ መስጠቱ እርሱ ለልጆቹ ርስት እንደሚሰጣቸው አባት ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በዙሪያችሁ ካሉ ከጠላቶቻችሁ ሁሉ ያሳርፋችኋል

“በዙሪያችሁ ካሉ ከጠላቶቻችሁ ሁሉ ሰላምን ይሰጣችኋል”

አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙ በዚያ እንዲቀመጥ በሚመርጠው ስፍራ ላይ

እዚህ ጋ “ስም” የሚወክለው እግዚአብሔርን ራሱን ነው። አ.ት፡ “አምላካችሁ እግዚአብሔር ለመኖር በሚመርጠው ስፍራ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእጃችሁ የምታቀርቡት ስጦታ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ሙሉውን ሰው። አ.ት፡ “የምታቀርቡት ስጦታ” (See: Synecdoche)

ስለ ስእለቶቻችሁ የተመረጡትን ስጦታዎቻችሁን በሙሉ

“ስእለታችሁን ለመፈጸም የምታቀርቧቸውን የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁን በሙሉ”