am_tn/deu/12/08.md

1.5 KiB

ዛሬ እዚህ የምናደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ ማድረግ የለባችሁም

“ዛሬ እዚህ እንደምናደርገው ማድረግ የለባችሁም”። ይህ ማለት በዚያ ወቅት ከሚያመልኩበት በተለየ ሁኔታ በተስፋይቱ ምድር ማምለክ ይኖርባቸዋል።

አሁን እያንዳንዱ የሚያደርገው በዐይኑ መልካም መስሎ የታየውን ነው

ዐይን ማየትን፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላል። አ.ት፡ “እያንዳንዱ የሚያደርገው ልክ ነው ብሎ የሚያስበውን ነው” ወይም “አሁን እያንዳንዱ የሚያደርገው ልክ ነው ብሎ የሚወስነውን ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ወደ ማረፊያ

“ማረፊያ” የሚለው የነገር ስም እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወደምታርፉበት ምድር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ርስት

እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ የሚሰጣቸው ምድር አባት ለልጆቹ እንደሚተውላቸው ርስት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ቋሚ ንብረት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ምድር” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)